ዴሞክራሲ ከማን ይጠበቃል??
ከ ነብዩ አለማየሁ ኦስሎ ኖርዌይ
ዴሞክራሲን ለማምጣት እርስ በእርስ መደማመጥና ሃሳብን በነፃ
ማንሸራሸርን ይጠይቃል ይሄ ዋና መሰረታዊ ነገር ንው።እስቲ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ እንዳስ በኢትዮዽያ የህውሀት መንግሥት
አመጣጡ እንደኔ ዓመለካከት ጥቂት የትግራይ ገበሬ ልጆች በኤርትራ የሻብያ እንቅስቃሴ በማየት ለምን እኛስ ሀገራችንን ትግራይን ነፃ
አናወጣም ብለው ነፍጥ ይዘው ጫካ ገቡ በጊዜው የደርግ መንግስት በብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮዽያዊያን የተቀጣጠለውን ዘውዳዊውን ስርኣት
አስወግዶ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲውተረተር የእንዚህ ጥቂት የዘረኝነት ዐባዜ የተፀናወታቸው ጥቂቶች ኣላማቸውን ለማሳካት ኣመቺ
ጊዜ ተፈጠረላቸው በተጨማሪም በወቅቱ ሿብያ በኤርትራ በኩል ያድርገው የነበረው ጦርነት የደርግን አትኩሮት በተሻለ መልኩ መሳቡ ተመቻቸው
በሶማልያ በኩል የሚካሄድውም ጦርንት ሌላው ምቹ ኣጋጣሚን ፈጥሮላቸው ነበር።
እነዚህም የትግራይ ልጆች በዙ ተባዙ በትግራይም ጫካዎች ውስጥ ተሰባሰቡ ነገር
ግን በህልምም ይሁን በውን በኢትዮዽያ ዴሞክራሲን ለማስፈን የህግ የበላይነትን ለማስከበር ኣላማ አልነበራቸውም በጭራሽ ኣላማቸው
ኣንድ ና ኣንድ ነበር የትግራይ ህዝብ ነፃ ኣውቺ ነበሩ ከእነርሱ ዴሞክራሲን መጠበቅ የማይታስ ነው።
የእውንቱ ሌላው
እይታ በትግራይ ጫካ የበዙት የቀድሞው ታጋዮች የደርግ መዳከም ምቹ አጋጣሚ ፈጠረላቸው ተከዜን ተሻገሩ ያኔ ኢትዮጵያን መቆጣጠር
እንደሚችሉ ሁኛ ሰው ከወደ UN ሹክ ኣላቸው ያኔማ ለኣማራው ፥ ለኦሮሞው ፥ ለቤሄሩ ሁሉ ተወካይ ፈላልገው ካገኙ ቡሃላ ሰተት ብለም ገቡ ። በስልጣን ለመቆየት አንዱን ብሄር ከሌላው ማጋጨቱን ተያያዙት
ከዚያም እነርሱ የተዋደቁለትን ዐላማ ማራመድ ጀመሩ የሃገሪቱን ዋና ዋና ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታነት በማዘዋወር ሰበብ ወሰዱ ትልቅ
የቢዝነስ ኢምፓየር አቋቋሙ ለኢትዮዽያ ህዝብም የይስሙላ ህገ መንግስት ጣል ተደረገለት እንርሱ ቀጠሉ መሠሎቻቸውን አምጥተው በመሀበር ቤት ስም ና በኮንዶሚኒየም
ስም ከተሙ።
ኢትዮጵያ ያሉ ጥቂት ጋዜጦችና
ፓርቲዎች ዴሞክራሲን እንፈልጋለ ሲሉ እሺ ይታሰብበታል በማልት ስራቸውን ቀጠሉ የሃገሪቱዋን መሬት ለበዓድ ሸጡ ተከታዮቻቸውን በሃገር
ውስጥና በውጪ ልከው አስተማሩ ኣላማቸውን የሚያሰናክልና ከእንርሱ ሃሳብ ውጪ የሆነውን ሁሉ ኣሰሩ ዓልያም ከሀገር አስወጥተው ለስደት
ዳረጉት ዋናውን ዓላማቸውን ኣልሳቱም የራሳቸውን ሰዎች ኑሮ ማሻሻልና በኢትዮዽያ የበላይ ሆኖ መታየት። እኛም ኧረ ዴሞክራሲ ኧረ
ነፃነት ኣልን ወይ ዴሞክራሲ ዓንዳንዶቹ እንዳውም ዴሞክራሲ ከፈለጋችሁ ጫካ ግቡ ማለት ጀመሩ በዚ መሃል ባዘጋጁት ምርጫ በተገኘች ትንሽ ክፍተት ያኔ የኢትዮዽያ ህዝብ እንድሚጠላቸው ግልብጥ ብሎ ውጥቶ ኣሳያቸው
ከዚያም ገድለውም ኣስረውም ገርፈውም ቢሆን ካረጋጉ ቡሃላ በውንም ይሁን በህልም ይህ ኣይነቱ ስተት ዳግመኛ እንደማይደገም ቃል ገብተው
እስከ መጨረሻው ጭላንጭሉን አዳፈኑት።
ሀይልማርያም ጠቅላይሚንስትር ሆነ ያኔ ከጀርባ ሆነው ኢኮኖሚውን ፥ መከላከያውን
፥ ደህንነቱንና ውጪጉዳዪን ህውሀቶች በመቆጣጠር እኛ ዴሞክራሲያዊነን በህጉ መሰረት የስልጣን ርክክብ ዓደረግን ኣሉን ታድያ እውነት
ከነኚህ የምንሻውን ዴሞክራሲ የሠፈንባት እኩልነትና የህግ የበላይነት
የተረጋገጠባት ኢትዮዽያን ከህውሀት መጠበቅ የዋሀንት ነው ። ካለን
ተሞክሮ እናም እንደኔ ሃሳብ ስልኛ ነፃነት ከኛ ሌላ ሊጮህልን የሚችል የለምና ልዩነታችንን አቻችለን ሁላችንም በትግላችን እንፅና።
No comments:
Post a Comment