Thursday, December 17, 2015

በጎንደር የልደታ ቤ/ክ ግምዣ ቤት በእሳት ጋየ

በጎንደር‬ ከተማ የልደታ ቤተ ክርስቲያን ዕቃ ግምጃ ቤት ሌሊቱን ሙሉ በሙሉ በእሳት ጋይቶ ወደመ፤ በቃጠሎው የህወሓት/ብአዴን እጅ እንዳለበት ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ናቸው ሲል የአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ዘገበ::
Zehabesha News
እንደራድዮው ዘገባ የጎንደር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የብአዴን ሹሞች በጠነሰሱት ስውር ሴራ በልደታ ቤተ ክርስቲያን የመሬት ይዞታ ላይ በ2001 ዓ.ም በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል የርስበርስ ግጭት እንዲፈጠር የሞከሩ ሲሆን አሁን ደግሞ አገዛዙ ከያቅጣጫው በችግር ስለተወጠረ በሁለቱም አስተዋይና በሳል የኃይማኖት አባቶች የተፈታውን ግጭት በመቆስቆስ እንደገና ለማገርሸት በማለም የዕቃ ግምጃ ቤቱን ሳያቃጥለው እንዳልቀረ የብዙዎች ግምትና ዕምነት ነው፡፡
በአዲስ አበባው አንዋር መስጊድ ለፈነዳው ቦምብም ህዝበ ሙሲሊሙም ሆነ ህዝበ ክርስቲያኑ ጣቱን ወደ ህወሓት እየቀሰረ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment