Tuesday, January 28, 2014

የለውጥ ሀይል ለሆነው ወጣት የተዘጉ ደጆች ይከፈቱ!!!

የለውጥ ሀይል ለሆነው ወጣት የተዘጉ ደጆች ይከፈቱ!!!
ከነብዩ አለማየሁ (ኦስሎ)
በሀገራችን ፖለቲካ አያሌ ክስተቶች ተስተናግደዋል እንደ መልካም ባሃል ልናጎለብተው የሚገቡ በርካታ ፖለቲካዊ አካሄዶች አሉ ከነዚም መካከል ዋናውና ወሳኙ አላማ ያልው ቁርጠኛ ተተኪን ማፍራትና እነኚህን ወጣት ፖልቲከኞችን ወደ ፖለቲካው ምህዳር ማምጣት። ወጣቱ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀላፊነት እንዳለው እንዲሁም ሀገራዊ ፍቅር ተስፋና ለሚፈጠሩ ለውጦች ወሳኝ የሆነውን ሚና ሊጫወት እንደሚችልና ቁርጠኛ አቋም እንዲይዝ የማድረግ ሀላፊነት ከፖለቲክኞቻችን የሚጠበቅ ወሳኝ ምግባር ነው።


ለአላማውና ለሀገር ፍቅር የቆመን ወጣት ለማፍራት በወያኔ የተሰሩ አልያም እየተሰሩ ያሉ መጥፎ ነገሮችን ብቻ መንገር በቂ አይሆንም ። ምንና እንዴት ለውጥን በምንሻት ሀገራችን ላይ ማምጣት እንዳለብን ማሳየት ሀሳቦችንና ልምዶችን በማጋራት  የተሻለ ነገን በሀገራችን የማምጣት ሀላፊነት በሁላችንም ዘንድ ይጠበቃል።
በሀገራችን ኢትዮዽያ በርካታ በገዥው መደብ እየተሰሩ ያሉ ሀገራዊ ማንነትን ሊሸረሽሩና ሊያጠፉ ሆን ተብሎ የተቀነባበሩ ሴራዎችን በምናይበት ወቅት በለውጡ ሂደት ላይ ወሳኝ ተሳትፎ ያልውን ወጣት ደጃችንን ከፍተን አቅሙ እንዲጎለብትና የወሳኙ  ሂደት ባለቤት ልናደርገው ይገባል  ነተጨማሪም በሃገራዊ ፍቅር በመቻቻልና ከብሄርተኝንት አስተሳሰብ የፀዳና  ወደ ብሄራዊ ስሜት እንዲመጣ የማድረግ ሀላፊነት የያንዳዱ ፖለቲከኛ  ተግባር ነው።
ሀገርን ማአከል አድርገው እየታገሉ የሚገኙ የፖልቲካ ድርጅቶችና መሪዎች  ሁሉ የተዘጉ ደጆቻቸውን የለውጡ ዋና ግብአት ለሆነው ወጣት ብሮቻቸውን  በመክፈት ቁርጠኛ የለውጥ ሀይሎችን በብዛት የማፍራት ሀላፊነት ይጠበቅባቸዋል። በተደጋጋሚ በፖለቲከኞቻን ላይ የሚታየው ግላዊ አመለካከትን በፓርቲና በአባላት ላይ ጭኖ ተግባራዊ የማድረጉ ጉዞ እስካሁን ላለንበት የፖልቲካ ሂደት  ያልበጀንና  የፍላጎታችንም ገደብ ውሰን ላለመሆኑ ማሳያ የሆነን  ተሞክሮነው።
በኢትዮዽያችን ፖለቲካ ለአንዳፍታ ቆም ብለን ስናስብ ሁላችንም በምንታገልላትና በምንሻት ሀገራችን ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን በነፃነትና በዕኩልነት የምንኖርባትን ኢትዮጵያን ለመገንባት ቀደምት ፖለቲከኞቻችን ያለፈውን የትግል ሂደት መልካሙን ከመትፎ በመለየት ለተተኪዎች አስተምሮና አሳይቶ በማፍል የምንመኛውን መልካም ለውጥ መስራት ኣልያም መቀየር ለሚችለው አካል በማስተላለፍ ታሪካዊ ሀላፊነታችንን መወጣት ይገባናል። በዘመናቸው  45 አመትና ከዚያም በላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ልክ አይደለም ዛሬ ደግሞ ጊዜው የሚፈቅደው አካሄድ ይሄ ነው ብሎ   የሌላውን የትግል  ሂደት ተስፋ አስቆራጭ ለማድረግ  መሞከር ሃላፊነት ከሚሰማው ለሃገርና ለህዝብ ነፃንት ቆሜያለሁ ከሚል የፖለቲካ ድርጅትና መሪ የሚጠበቅ አስተያየት አይመስለንም። በቅርቡ አቶ ሌንጮ ወደ ሀገር ቤት የመግባት እቅዳቸውን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት የሌላውን የትግል  ሂደት ከጥያቄ ውስጥ ለማስገባት  ለማጣጣልና ተስፋ አስቆራጭ ለማድረግ  የተደረገ ይምስለኛል።   ነገር ግን እርሳችው ብቆዩባቸው በርካታ አመታት ውስጥ  ታላቅ የተሰኙ ለችውጦች  በሀገራችን ውስጥ ተከስተዋል በነኚህ ትልግሎች ውስጥ እርሳችው የሚመሩት ድርጅት የለውጡ ባለቤት ያልሆነበትን ምክንያት መመርመር ከዚያም ለተተኪዎች እድሉን መስጠት  በተሻለ መልኩ ለውጡን ሊያመጡ የሚችሉት ሀይሎች ላይ ጊዜን እቅምን በማጎልበት ከመሪነት ወቶ ወይም በጡረታ ተገልሎ በማማክር የስራ ዘርፍ እንደሌላ የትግል ዘርፍ በማየት ሂድቱን ማጎልበት  የሚገባ ሲሆን አልያ በአመራር  ለመቆየት ሲባል በየጊዜው የፖለቲካ ፓርቲዎችንና አጀንዳዎችን ማዘጋጀት ለውጥንና ነፃነትን የናፈቀውን ህዝባችንን ወደዋላ መጎተት ነው። ከምንም በላይ በተለያየ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥና የትኛው የፖለቲካ ድርጅት እውነት ለሃገራችን ለውጥ ለማምጣት የያንዳንዳችንን አስትዋፆ የሚሻው የለውጥ ሃይል የትኛው ነው ብሎ በማሰብ ላይ ላለው ወጣት ተስፋ አስቆራጭ እንዳይሆን ቆም ብሎ ማስቡ መልካም ነው።


ወጣቱ በአሁኑ ጊዜ  የሚፈልገው ቁርጠኛና ከመሬት የወረደ ትግል ነው። መሪዎቻችን በሀላፊነት መምራትና የለውጡ ሀዋርያ እንዲሆን ደጆቻችንን ከፍተን ታሪካዊ ሃላፊነታችንን ታሪክ በመስራት እንወጣ::

No comments:

Post a Comment